የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን ይፋዊ ጉብኝት ሊያደርግ ነው

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጦርነት ክፉኛ በተጎዳችው የመን ይፋዊ ጉብኝት ሊያደርግ ነው

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የተከሰተዉን ጦርነት ተከትሎ እንደአውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2014 ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በየመን ሰነአ እግሩን ያሳረፈው፡፡

የሁቲ ታጣቂዎች መስራች የሆነው ኢራናዊው ሁሴን በድረዲን ለይቶለት የሁቲ ታጣቂዎችን በይፋ ሲቀላቀል እና ሰነኣን ሲቆጣጠር ጀምሮ ነው ድርጅቱ ልዩ መልዕክተኛዉን ወደ ስፍራው እየላከ የተኩስ አቁም ስምምነት ሲያደረግ የነበረው፡፡

በተለይም በየመኗ የወደብ ከተማ ሆዳድ ላይ የተደረገው ጦርነት ስምምነቱ ሲጣስ እና የደርጅቱ ልፋት ከንቱ ሲደረግ ለመቆየቱ ማሳያ ነው፡፡

አሁንም በማርቲን ግሪፊን የሚመራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልኡካን ቡድን በየመን ዘላቂ ሰላምን ለማረገገጥ የሚያደርገዉን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡

ለዚህ ማረጋገጫው ደግሞ አሁንም በዚሁ ግለሰብ የሚመራው ልዩ የልኡካን ቡድን ወደየመን ሊያቀና ነው፡፡

ይህ ቡድን የወደብ ከተማዋን የጉብኝቱ አካል እንደሚያደርገው አስታውቋል፡፡

ከ10 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈው እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን በሞት እና ህይወት መካከል እንዲኖሩ ያደረገው የየመኑ የእርስ በርስ ግጭት ያበቃ ዘንድ ጥረቶች በተደጋጋሚ ቢደረጉም ይጣሣሉ እንጅ አይፀኑም፡፡

የልኡካን ቡድኑ መሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፍ በተለይም ላለፉት ሁለት አመታት ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ይነገራል፡፡ ይሁን እንጅ ተሳክቶላቸው አያውቅም፡፡

አሁን የተሰነቀው ተስፋ ምናልባት ድርጅቱ የስኬት ተስፋ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም የማርቲን ወደ ስፍራው መጓዝን ተከትሎ መግለጫ የሰጠው የሁቲ አማፂያን ቡድን ከፍትኛ መሪ እና አቢዮታዊ አራመጅ የሆነው ሞሃመድ አሊ አል ሁቲ የልኡካኑን በሆዳድ መገኘትን ተከትሎ ከዚህ በኋላ ወታደራዊ ግጭት እንደማይባባስ ተስፋ አለኝ ሲል መግለጹን የአልጄዚራ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ማርቲን ግሪፍ በበኩላቸው በየመን የሚገኙ የኣማፂያን መሪዎች የሰላም ምክረ ጉባኤን ለመከታተል እና ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ከከዚህ ቀደሙ በተለየ ሁኔታ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሀገሪቷ ውስጥ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ፍላጎት እንዳላቸው እና ይህም የሚሆን ከሆነ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ጽኑ ፍላጎት አላቸው ያሉት የልኡካን ቡድኑ መሪ ማርቲን ግሪፍ ናቸው፡፡

ይህ ደግሞ የማርቲንን ጉዞ የተስፋ ጭላንጪል እንዲኖረው ያደርገዋልም ነው የተባለው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን ተስፋ ሰንቆ ይራመድ እንጅ አንዳንድ የፖለቲካ ምሁራን እና የመገናኛ ብዙሃን በቀይ ባህር ላይ ትኩረት ያደረገው የሆዳዱ ጦርነት ከስምምነቱ ማፈንገጡ አይቀርም ማለታቸዉ እየተነገረ ነው፡፡

ምክኒያቱ ደግሞ የወደብ ከተማ እና ዓለም አቀፍ የንግድ ቀጠና የሆነቸው ሆዴድ ከተማ በአማፂያንም ሆነ በመንግስት የምትፈለግ ከተማ ነች እና፡፡

ይህ ሁኔታ የድርጅቱን ተስፋ አጣብቂኝ ውስጥ ሊያስገባው ይችላል የሚለው በስጋትነት የሚነሳ ሲሆን ምናልባት ግን የአሁኑ የመንግስታቱ ድርጅት ጥረት ተሳክቶ ያች ሃገር የሰላም አየር ልትተነፍስ ትችላለች የሚለውም በሌላ በኩል እየተስተጋባ ይገኛል፡፡