እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት የምታደርገውን ጉዞ አብዛኛዎቹ የምክር ቤት አባላት ደገፉት

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት የምታደርገውን ጉዞ 200 የምክር ቤት አባላት ሲደግፉት 117ቱ ተቃውመውታል፡፡

እንግሊዝ እ.አ.አ በ2016 ያደረገችውን ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ ሁለት ዓመታን የፈጀው ከአውሮፓ ህብረት የመውጣት ሂደት አሁን ላይ ወደ መጨረሻው የተቃረበ ይመስላል፡፡

በአንዳንድ ፀሐፍት እና የፖለቲካ ተንታኞች ከህብረቱ የመውጣት ፍላጎቱ እንደማይሳካ እና አገሪቱ ብትወጣ እንኳ የከፋ ችግር ላይ ልትወድቅ እንደምትችል ቅድመ ትንበያ እና ሀሳብ ሲሰጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ለዚህ በቂ ዝግጅት አድርጊያለሁ የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ መንግስት በምክር ቤቱም ጭምር የከበደ ተጽእኖ ሲደርሰበት ነበር፡፡

አስፈላጊው ቅድመ ጥናት እና ምጣኔ ሀብታዊ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት አጋማሹ እና ተጠባቂው ውሳኔ የምክር ቤቱ ድምጽ ነበር፡፡    

ምክር ቤቱም ለእኩል ተከፍሏል ሲባል እንዳልነበር በትናንትናው እለት በምስጢር በተሰጠው ድምጽ የሜይ ሀሳብ የበላይነትን ይዞ ተጠናቋል፡፡

200 አባላቱ የደገፉት ከህብረቱ የመውጣት ፍላጎት በአውሮፓ ህብረት እና በህብረቱ አባል አገራት እንዲሁም በአንዳንድ ዓለማቀፍ ተቋማት ያልተጠበቀ ቢሆንም፤ ሜይ ይህን ውሳኔ ይዘው በህብረቱ ጉባኤ ላይ ለመካፈል እንደሚጓዙ የመገናኛ ብዙሃኑ እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡

የአሁኑ የህብረቱ ጉባኤ የእንግሊዝን አቋም በሚገባ እንደሚፈትሽ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ሜይ በ27 የህብረቱ አባል አገራት ፊት፤ ባሉ መልካም አጋጣሚዎች እና ቀጣይ ፈተናዎች ላይ ፊት ለፊት ይነጋገራሉ፡፡

ህብረቱም ባለፉት ጊዜያት ያረቀቃቸውን የግንኙነት መርሆችን ዳግም እንደሚያሻሽልም ይጠበቃል፡፡  ይህ ማለት የሚጨመሩ እና የሚቀነሱ የህግ እና የግንኙነት ማዕቀፎች እንዲሁም የልዩነት ድርሻዎች በግልጽ ይቀመጡበታል፡፡

አሁን የእንግሊዝ መንግስት ወደ ፈተና የሚገባበት ሰዓት የደረሰ ይመስላል፡፡ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት አብዛኛው ስራ ወይንም ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ እንግሊዛውያኑ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡

የህግ ማዕቀፎቻው አገሪቱ ከህብረቱ ጋር የሚኖራትን ግንኙነት እና ከሌሎች አገራት ጋር በንግድ ኢንቨስትመንትና ዲፕሎማሲው ዘርፍ የሚኖራትን ድንበር የሚያበጅ ነው፡፡

ይህ ሲጠናቀቅ ህብረቱ የመለያየት ምዕራፉን ያከናውናል፡፡ ይህ ጊዜ የአባል አገራቱ ለመጨረሻ ጊዜ ድምጽ ሰጥተውበት ውሳኔ የሚያስተላልፉበት ነው፡፡ ነገር ግን የህብረቱ ድምጽ ያን ያህል ለውጥ የሚያመጣ እንደማይሆን ይታመናል፡፡

የህብረቱን ድምጽ መሠረት አድርጎ ተፈፃሚ ከሚሆነው መለያየቱ በኋላ የመጨረሻው የንግድ ግንኙነት ውይይት እና ሽግግር ሲሆን እስከ ቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ ድረስ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሂደቱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከተከናወነ በ2020 እንግሊዝ ከህብረቱ አባልነት ሙሉ በሙሉ መውጣቷን ታረጋግጣለች ማለት ነው ቀጣዩ አጠቃላይ አገራዊ ምርጫም በ2022 ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ውጭ በአገሪቱ ይከናወናል፡፡