እስራኤል በሀማስ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች

እስራኤል በጋዛ በሚገኝ የሀማስ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች፡፡

እስራኤል የአየር ድብደባውን የፈፀመችው ሀማስ በሰሜናዊ የቴላቪቭ ከተማ የሚገኝ ቤትን በሮኬት መምታቱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በሀማስ የሮኬት ጥቃት 7 እስራኤላውያን መቁሰላቸውን የአገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡

በአፀፋው እስራኤል በወሰደችው የአየር ጥቃት 7 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን የሀማስ የፖለቲካና ወታደራዊ ዋና መስሪያ ቤት መውደሙ ተነግሯል፡፡

እስራኤል ይህን የአየር ጥቃት የፈፀመችው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አሜሪካ በሄዱበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ የሀማስ ድርጊትን ኮንነው ሀገራቸው እንደዚህ ዓይነት ጥቃትን እንደማትታገስ ተናግረዋል፡፡

ኔታኒያሁ በአሜሪካ ቆይታቸው የሶሪያ ግዛት እንደሆነ የሚነገረውን የጎላን ኮረብታ የእስራኤል ልኡዋላዊ ግዛት መሆኑን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በይፋ አስታውቀዋል፡፡

(ምንጭ፦ቢቢሲ)