ሩሲያ የደቡብ ኮሪያ የአየር ክልል መጣሷን ተከትሎ ይቅርታ ጠየቀች

የሞስኮ የአየር ሃይሎች ሁለት ጊዜ የሴዑልን አየር ክልል በመጣሳቸው ደቡብ ኮሪያ በሩሲያ ላይ ክስ አቅርባለች፡፡ ምንም እንኳን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ድርጊቱ አልተፈጸመም ሲል በወቅቱ ቢያስተባብልም፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አክሎም በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የሞሰኮ-ቤጂንግ የአየር ወታደራዊ ስልጠናው በጃፓን ባህር እና በምስራቅ ቻይና ባህር ላይ የተደረገ ነው ሲል አስረግጦ ተናግሯል፡፡

እንደ ደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ማብራሪያ ግን ሶስት የሩሲያ እና ሁለት የቻይና ወታደራዊ ሄሊኮፍተሮች ለሁለት ጊዜ ያህል የኮሪያውን የአየር ማስጠንቀቂያ ክልል ውስጥ ማክሰኞ ማለዳ ውለው ነበር፡፡ ኤ-50 የተሰኘው የሩሲያ የጦር አውሮፕላንም ለሁለት ጊዜ የአየር ክልሉን ጥሶ ገብቷል፡፡

ሩሲያ የሲዑልን አየር ክልል የጣሰችው ሆንብላ ባለመሆኑ ይቅርታ መጠየቋንም ነው የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ያስታወቁት፡፡

የሩሲያ እና ቻይና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች በቅርብ ጊዜያት በሚያደርጉት ስልጠና የሃገራት ድንበር ሲጥሱ ቢስተዋልም ከኮሪያ ጋር መሰል እሰጣ ገባ ውስጥ ሲገቡ መጀመሪያው ነው፡፡