ፓኪስታን ከህንድ የካሽሚር ውሳኔ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ ቻይና ላከች

የፓኪስታኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ ሙሀሙድ  ህንድ በካሽሚር ግዛት ያሳለፍችውን ውሳኔ እንድትቀለብስ ለመድረግ ያለመ ጉዞ ወደ ቻይና አድርገዋል፡፡

በቻይና ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ነው የሚጠበቀው።

የአሁኑ  የህንድ ውሳኔ ከፍተኛ  የፖለቲካ ትኩሳት በነገሰበት አካባቢ ባለፉት ሰባት አስርት ዓመታት ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ጠንካራው እንደሆነም ፖለቲከኞች ይናገራሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ፓኪስታን ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገልጻለች።

ህንድ በቅርቡ የሻረችው አንቀፅ 370 የካሽሚር ግዛት የነበረውን የራስ ገዝ አስተዳደር እና ህግ የሚያግድ ሲሆን፤ ውሳኔውን ተከትሎ ህንድ በርካታ ወታደሮችን ወደ አካባቢው በማሰማራት ፖለቲከኞችን አስራለች፣ የኢንተርኔት እና  የስልክ ግንኙነትም እንዲቋረጥ አድርጋለች፡፡

ይህ ውሳኔ ወትሮም ሻክሮ የቆየውን የሁለቱን  ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ወደ ውጥረት  ከቶታል፡፡

 ህንድ ለካሽሚር ግዛት ልዩ መብት የሚሰጠውን ህገ መንግስታዊ ውሳኔ እንዲሻር ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ