ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን የእንግሊዝን የህዝብ እንደራሴዎች ከስራ ለማገድ ማቀዳቸው ቁጣ ቀሰቀሰ

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የእንግሊዝን የህዝብ እንደራሴዎች ከስራ ለማገድ ማቀዳቸው በሀገሪቱ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡

የሀገሪቱ ንግስት ኤልዛቤት ሁለተኛ ውሳኔውን እንዲያጸድቁት ጥያቄው ይቀርብላቸዋል ተብሎ እየተጠበቀ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ  በንግስቲቱ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጥቅምት ላይ ሀገሪቱን ከአውሮፓ ህብረት ያለምንም ድርድር ለመነጠል የተያዘው የጆንሰን እቅድ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከባድ ፈተና የሚደቅን መሆኑ በበርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች፣ ፖለቲከኞችና ሌሎች ባለሙያዎች እየተተቸ ቢሆንም ቦሪስ ጆንሰን እቅዳቸውን ከማስፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ እየተናገሩ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የያዙት ፓርላማውን ከስራ የማገድ እቅድ ከፓርላማው አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡

ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡