በካቡል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል በተፈጸመ ጥቃት 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።

ለጥቃቱ የታሊባን ታጣቂ ቡድን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ታሊባን በቅርብ ቀናት ውስጥ ብቻ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ሃላፊነቱን ሲወስድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡

በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የእርዳታ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንደሆነ የተነገረው አካባቢው በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሆኗል፡፡

 ምንጭ፦ አልጀዚራ