የሮሂንጊያ ማህበረሰብ መንደር ሙሉ በሙሉ ለመንግስት የልማት ተቋማት መዋሉ ተገለፀ

በማይናማር የሮሂንጊያ ማህበረሰብ መንደር ሙሉ በሙሉ ለመንግስት የልማት ተቋማት መዋሉን ቢቢሲ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ባንድ ወቅት የሮሂንጊያ ማህበረሰብ መኖሪያ የነበረው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ የመንግስት የልማት ተቋማት እንደተገነቡባቸው በሳተላይት ምስሎች ማረጋገጡን ነው  ቢቢሲ የገለፀው፡፡

አካባቢው አሁን ላይ የፖሊስ ፅህፈትቤት፣ የስደተኞች ማቆያን በመሳሰሉ የማይናማር መንግስት ግንባታዎች  መሞላቱም ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳን የአካባቢው ባለስልጣናት ግንባታውን ቢያስተባብሉም፡፡

እ.አ.አ በ2017 በማይናማር የሚገኙ ከ700 ሺህ በላይ የሮሂንጊያ ማህበረሰብ አባላት ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ሀገሪቱ በሮሂንጊያ ማህበረሰብ አባላት ላይ ከበቂ በላይ ወታደሮችን በመጠቀም ግድያ በመፈፀም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ማድረጉም አይዘነጋም፡፡

በአብዛኛው የቡድሂት እምነት ተከታዮች የሚገኙባት ማይናማር በአንድ ወቅት በዚሁ ማህበረሰብ ላይ በዘር ማጥፋት ተጠያቂ ተደርጋ የነበር ሲሆን አሁን ደግሞ ስደተኞችን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን በጸደጋጋሚ እየገለፀች ትገኛለች፡፡

ምንም እንኳን ከ3 ሺህ በላይ የሮሂንጊያ ማህበረሰብ አባላት ወደ ቀደመ ቀያቸው ለመመለስ ያደረጉት ጥረት ባይሳካም፡፡