የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሳዑዲ አረቢያ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ መመታቷ ተነገረ

የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ በቀይ ባህር ሳዑዲ አረቢያ አቅራቢያ በሮኬት ተመትታ መጋየቷን የኢራን ሚዲያዎች ገልፀዋል።

ንብረትነቷ የኢራን ብሄራዊ የነዳጅ ኩባንያ እንደሆነ የተገለፀው ነዳጅ ጫኝ መርከብ የሳዑዲ የወደብ ከተማ ከሆነችው ጀዳ 97 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በእሳት መያያዟን የኢራን ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ አስታውቋል።

መርከቧ በሽብርተኞች በተፈፀመ ጥቃት በእሳት ሳትያያዝ እንዳልቀረ  ተገምቷል፡፡

ፍንዳታው በመርከቧ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ጭናው የነበረው የነዳጅ ዘይት ወደ ባህሩ እየፈሰሰ እንደሚገኝ የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ