የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ባካሄደው ምርጫ ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም ድርጅቱን ለመምራት ከሚፎካከሩት የመጨረሻዎቹ ሶስት ዕጩዎች ውስጥ መካተታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ ።
የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላቱ ለድርጅቱ ዋና ዳይሬክተርነት በአባል አገራት ከቀረቡ እጩዎች ውስጥ ሁለተኛ ማጣሪያ ምርጫቸውን ናንት ሌሊቱን አካሂደዋል ።
ቦርዱ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች ለመለየት ባካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ኢትዮጵያንና አፍሪካን ወክለው የቀረቡት ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም መምረጡን ነው ያስታወቀው ።
ከዶክተር ቴድሮስ በተጨማሪ ለግንቦቱ መጨረሻ ውድድር የቀረቡት ሁለት ዕጩዎች ዶክተር ዴቪድ ናባሮና ዶክተር ሳኒያ ኒሽታር የተባሉ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
የቦርዱ ስራ አስፈፃሚ አባላት ሶስቱን ተፎካካሪዎች ቃለ መጠይቅ በማድረግ ነበር ይፋ ያደረገው ።
ለነዚህ እጭዎችም አባል አገራቱ የፊታችን ግንቦት በሚያካሄዱት ጠቅላላ ጉባኤ በቀጥታ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር የሚሆነውን አሸናፊ እንደሚለዩ አመልክቷል ።
ተመራጩ ዋና ዳይሬክተር ደግሞ እ ኤ አ ከሐምሌ 1/2017 ጀምሮ መደበኛ ስራውን እንደሚጀምር መገለጹ ይታወቃል ።