ሎስ አንጀለስ ከተማ ከፍተኛ ሙቅትን ለመቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመረች

የአሜሪካዋ ከተማ ሎስ አንጀለስ በከተማዋ በበጋ ወቅት ያለውን ከፍተኛ ሙቀት ለመቀነስ የሚያስችል ለየት ያለ ተክኖሎጂ መጠቀም ጀመረች።

ይህም ቴክኖሎጂ የከተማዋን ጥቁር አስፓልቶች በተለየ መልኩ ግራጫ ቀለም ያለው ቅባት በመቀባት የከተማዋን ከፍተኛ የሙቀት መጠን እየቀነሰች ነው ተብሏል፡፡  

በሎሳንጀለስ ከተማ የበጋው ወቅት በሚመጣበት ጊዜ የከተማዋ የሙቀት መጠን 38 ዲግሪ ሴሊሺየስ የሚደርስ ነው ተብሏል፡፡

ይህም  ሙቀት ነዋሪዎች ያለ ማቀዝቀዣ እንዳይንቀሳቀሱ እና በዚህም ምክንያት በጋ በመጣ ቁጥር ለከፍተኛ ወጪ እንዲዳረጉ እያደረገ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ሎስአንጀለስ ይህን ሙቀት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ያስችላል ያለችውን ቴክኖሎጂ መተግበር ጀምራለች፡፡

ይህም  ቴክኖሎጂ ግራጫ ቀለም ያለው ልዩ ቅባት መሳይ ነገር የእግረኛ መንገዶችን እና ጥቁር አስፓልቶችን በመቀባት ሙቀቱን መቀነስ ያስችላል ነው የተባለው ፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማንኛውም ጥቁር አስፓልት ከ80 እስከ 95 በመቶ ያህል የፀሀይ ሙቀትን የሚመጥ ሲሆን ይህ አዲሱ ግራጫ መሳይ የአስፓልት ቅባት ግን በኮንክሪት መልኩ የተሰራ ሲሆን ከፀሀይ የሚመጣዉን ከፍተኛ ሙቀት የማይመጥ እና አንፀባርቆ ብቻ የሚመልስ ነዉ፡፡

እንዲሁም  ከበፊቱ  ጥቁር አስፓልት በተሻለ  የመሬት ዉስጣዊ የሙቀት መጠን ዝቅተኛ እንዲሆን እና የከተማዋ ፀሀያማ ቦታዎች የሙቀት መጠናቸዉ እንዲቀንስ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የአሰፓልት ቅባቱ የከተማዋን የሙቀት መጠን ከነበረበት የ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በ 11ነጥብ1 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን የካሊፎርኒያ ግዛት ይፈጠር በነበረው ሙቀት የተናሳ በተደጋጋሚ ይከሰት የነበረውን የእሳት አደጋ እንዲቀር እንደሚያደርግም ተስፋ ተደርጎበታል፡፡

የከተማዋ የጎዳና አገልግሎቶች ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር ግሬግ ስፖትስ በበኩላቸው ቴክኖሎጂውን በመኪና ማቆሚያ መንገዶች ላይ እና ቀጥሎም በእግረኛ መንገዶች ላይ የተገበረች የመጀመሪያ ከተማ ሎስአንጀለስ መሆኑዋን ገልጻው ሌሎች ከተሞችም ይህን ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ እየገፋፋን ነዉ እናም የዚህ ቴክኖሎጂ አምራቾች ተጨማሪ አዳዲስ ምርቶችን እንደሚያቀርቡ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

በሎስ አንጀለስ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ  የአካባቢ  የተፈጥሮ  ሳይንስ ፕሮፌሰር  የሆኑት  አሊን  ባሬካ  ከአየር  ማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂ (አየር ማቀነባበሪያ) እና ከመሳሰሉ  የአሠራር  ዘዴዎች ይበልጥ ይህ ግራጫ መሳይ የአሰፓልት ቅባት በተሻለ መልኩ ሙቀቱን ሊቀንስ  እንደሚችል ተናግረዋል፡፡.

የሎስአንጀለስ ከተማ  የአራት ሚሊየን ዜጎች መኖሪያ መኖሪያ ስትሆን ይህን መሳይ ለየት ያለ የሙቀት መቀነሻ ቴክኖሎጂ የተጠቀመች የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማም አድርጓታል፡፡ 

ይህ ግራጫ የአሰፓልት ቅባት በነባሩ ጥቁር አስፓልት ላይ በተቀባ በ 30 ሴኮንድ ውስጥ የሚደርቅ ሲሆን ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ጥቅም እንደሚሰጥ  በዘገባው አትቶታል( ሲጂቲኤን )