በግሪክ የተገኘው የራስ ቅል አውሮፓ በኒያንደርታሎች በተወረረችበት ወቅት 210 ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ነው ተብሏል።
ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው፤ የሰው ልጅ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ቅድመ ፍልሰት ስለማድረጉ ታሪክ ምንም አይነት የዘረመል ማስረጃ የለውም ለሚለው ሌላ አስረጅ ሆኖ ቀርቧል።
ይህ ግኝት የታተመው 'ኔቸር' በተሰኘው ጆርናል ላይ ሲሆን፣ ተመራማሪዎች በ1970ዎቹ በግሪክ አፒዲማ ዋሻ ውስጥ ሁለት ጠቃሚ ቅሪተ አካል አግኝተው እንደነበርም ተገልጿል።
አንዱ በጣም የተዛባ ሌላኛው ደግሞ ያልተሟላ የነበር ቢሆንም ተመራማሪዎች የተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የቅሪተ አካሉን ምስጢር ሊደርሱበት ችለዋል።
ይህም ተመራማሪዎቹ በግሪክ ከዛሬ 210 ሺህ ዓመት በፊት ጥንታዊ ሰው በርከት ብሎ ይኖር ነበር እንዲሉ አስችሏቸዋል።
ከአፍሪካ ውጪ የሚገኘው የዓለማችን ሕዝብ ከየት መጣሁ? ብሎ ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ ከአፍሪካ መፍለሱን ይናገራል።
መቼ? ለሚለው ደግሞ ከ60 ሺህ ዓመት በፊት የተመራማሪዎች መልስ ነው።
ይህ ዘመናዊ ሰው ወደ አውሮፓና እስያ ሲሄድ በመንገዱ ላይ ያገኛቸውን እነ ኒያንደርታልና ዴኒሶቫንስን እየተኩ መሄዳቸው ይታመናል።
ነገር ግን ዘመኑ ጥንታዊ ሰው (ሆሞሳፒያንስ) ከአፍሪካ ወደ ሌሎች የዓለማችን ክፍል መፍለስ የጀመረበት የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም።
የሆሞሳፒያንስ ቅሪተ አካል በ1990ዎቹ በእስራኤል ከስኩሁል እና ቃፍዜህ የተገኘ ሲሆን፤ እድሜውም ከ90 ሺህ እስከ 125 ሺህ ድረስ ተገምቷል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጥንታዊ ሰው ከአፍሪካ ወደ አውሮፓና ወደ እስያ ያደረገውን ፍልሰት በሚመለከት የሚደረጉ ጥናቶች ላይ አንዳንድ ፍንጮች እየተገኙ መሆናቸውን ተመራማሪዎች ያስረዳሉ።
ቻይና ውስጥ በዳኦክሲያንና ዝሂሬዶንግ የተገኘው ቅሪተ አካል እድሜው በ80 ሺህና በ120 ሺህ መካከል ተገምቷል።
የዘረመል ጥናቶች ላይ ምርምር የሚያደርጉ ሰዎች ከአፍሪካ የሄዱና ኒያንደርታሎች ተዳቅለው አግኝተናል ብለዋል።
በጀርመኖቹ የኒያንደርታሎች መዳቀል የተፈጠረው 219 ሺህ እና በ460 ሺህ ዓመታት መካከል ነው።
ነገር ግን አሁንም ሆሞሳፒያንስ መዳቀሉ ላይ ተሳትፈውበታል ወይስ ሌላ ጥንታዊ የአፍሪካ ቡድን አለ ለሚለው መልስ አልተገኘለትም። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)