በፈረንሳይ ባሮኒስ ግዛት ከሁለት ዓስርት ዓመታት በፊት የተጀመረው የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራ በአነስተኛ የግብርና ምርቶች ብቻ ጥገኛ የነበሩትን የአካባቢው ነዋሪዎች በቱሪዝም ገቢ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል።
በፈረንሳይ የባሮኒስ ግዛት የአካባቢ መራቆት ያሳሰባቸው የአካባቢው ተቆርቋሪዎች ከሁለት ዓስርት ዓመታት በፊት የጀመሩት የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራ በአነስተኛ የግብርና ምርቶች ብቻ ጥገኛ ለነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎችም ከቱሪዝም ገቢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡
ከሁለት አስርተ አመታት በፊት አካባቢውን በመከለል የተፈጥሮ ሐበት ጥበቃ ስራ በመስራት አካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ በሚል የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ፍሬ አፍርቷል ተብሏል፡፡
አካቢውን ፓርክ ለማድረግ ጥብቅ ህግ በማውጣት ከፍተኛ የእንክብካቤ ያደረጉት የአካባቢው ነዋሪዎች ተራራማ አካባቢያቸውን ውበት አላብሰው ከቱሪዝም ገቢው ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ዘ-ኢኮኖሚስት ዘግቧል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የተፈጥሮ ሐበት ጥበቃ ስራው እውቅና አግኝቶ የባሮኒስ ግዛት አስተዳደር ፓርክ በፈረንሳይ ከሚገኙ ጥብቅ ፓርኮች መካል አንዱ ለመሆን ችሏል ነው የተባለው፡፡
በመሆኑም በአነስተኛ የግብርና ምርቶች ብቻ ጥገኛ ለነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎችም ቱሪዝም ሌላ የገቢ ምንጭ ሆኗቸዋል ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2015 51ኛው በፈረንሳይ የባሮኒስ ፓርክ በሚልም እውቅና አግኝቷል። ፓርኩ 1ሺ800 እስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ሲኖረው፤ ጥቅጥቅ ደን እና ተፈጥሯዊ ፏፏቴዎችን በውስጡ መያዝ ችሏል፡፡
በተደረገው የተፈጥሮ ሐብት ስራ ፓርኩ ለተራራ መውጣት፣ ለብስክሌት ውድድር፣ ለፈረስ ግልቢያና ለመሳሳሉ ስፖርታዊ ውድድሮች በፈረንሳውያን ዘንድ ተመራጭ ፓርክ ለመሆን ችሏል፡፡
እነደ ዘ-ኢኮኖሚስት ዘገባ ይህ በባሮኒስ አስተዳር የተከናወነው ውጤታማ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ፤ ፈረንሳይ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያከናወነችው ስኬታማ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ማሳያም ተብሏል ፡፡
በፈረንሳይ እ.ኤ.አ 1990 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የአካባቢ እንብካቤና የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራ የሀገሪቱን የደን ሽፋን በሰባት በመቶ እንዲጨመርም አድርጎታል፡፡ይህም ከጥቅል ከሀገሪቱ የቆዳ ስፋት ውስጥ የደን ሽፋኑን ወደ 31 በመቶ እንዲያድግ አድርጎታል፡፡ይህም ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ፈረንሳይን 4ተኛዋ ሰፊ የደን ሽፋን ያላት ሀገር ያደርጋታል፡፡ ስዊዲን፣ ፈንላድና ስፔን በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ተኛ ያለውን ደረጃ ይይዛሉ፡፡
የደን ልማት ስራ ውጤቱን የፈረንሳይ ብቻ ሳይሆን የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሚጋሩት ስኬት መሆኑን የዘገበው የዘ-ኢኮኖሚስት፤ የህብረቱ አባላት ባለፉት 25 ዓመታት በጥቅል ውጤታማ የደን ልማት ስራ አከናውነዋል ብሏል፡፡
በአውሮፓ ህብረት ሀገራት መካከል በጥቅል ከ1990 እስከ 2015 በተሰራው ውጤታማ የተፈጥሮ ሐብጥ ጥበቃ ስራ የአካባቢው የደን ሽፋን በ90ሺ000 ስኩየር ኪሎ ሜትር እንዲጨምር አስችሏል፡፡ይህም የህብረቱ ሀገራት ባለፉት 25 ዓመታት የፖርቹጋልን የቆዳ ስፋት የሚያክል መሬት በደን መሸፈን መቻላቸው ነው የተዘገበው፡፡
ከአውሮፓ ሀገራት በደን ሽፋን ቀዳሚ የሆነችው ስዊዲን ከቆዳ ስፋቷ 28 ሚሊዮን ሄክታር መሬቷ በደን የተሸፈነው ሲሆን፤ ይህም የሀገሪቱን 68.9 በመቶ ቆዳ ይሸፍናል፡፡ ፊንላንድ 22 ሚሊዮን ሄክታር፣ ስፔን 18.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬታቸው በደን የተሸፈነ ነው፡፡
በአህጉረ አውሮፓ ባፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከኢንዱስትሪያል የኢኮኖሚ መሰረታቸው ጎን ለጎን የአካባቢ እንክብካቤና የደል ልማት ስራ ቀዳሚ ተግባር በማድረግ አበክረው ሰርተዋል፡፡
በአንጻሩ በጥቅል በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ 1990 ጀምሮ በአፍሪካ ደረጃ የእጽዋት ሽፋን እየተመናመ መሆኑ ነው ዘኢኮኖሚስት የሚያትተው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እ.ኤ.አ ከ1990 እስከ 2016 የደቡብ አፍሪካን የቆዳ ሽፋን የሚያክል ማለትም 1.3 ሚሊዮን ስኩየር ኪሎ ሜትር ደን ወድሟል ተብሏል፡፡
በአፍሪካ ከባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ወዲህ የሙቀት መጨመር፤ የዝናብ እጥረት ድርቅ እና ረሀብ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተከሰቱ መሆኑን ዘ- ኢኮኖሚስት ጠቅሷል፡፡