በባሀማስ የተከሰተው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ አሜሪካ እያቀና ነው ተባለ

ባሀማስን የመታው ሀሪኬን ዶሪያን የተሰኘው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ አሜሪካ እያቀና መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም ለ20 ሰዎች ህልፈት መንስኤ የነበረውና ሀሪኬን ዶሪያን የሚል መጠሪያ ያለው ይህ ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ  በተመሳሳይ በአሜሪካ ሊከሰትና ለሰዎች ህልፈት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል።

የባሃማሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁቤርት ሚኒ ሀሪኬን ዶሪያን ሀገሪቱን ካጋጠሙ ተፈጥሯዊ አደጋዎች በታሪክ ትልቁን ስፍራ የሚይዝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አውሎ ንፋሱ በሃማስን ከመታ በኋላ ፍጥነቱ ተቀዛቅዞ እንደነበረ ቢገመትም አሁን ላይ  ፍጥነቱን ጨምሮ ወደ አሜሪካ እያመራ ነው ተብሏል።

እንደ የአሜሪካ ሀሪኬን ማዕከል ከሆነ ሀሪኬን ዶሪያን በአሁኑ ወቅት በጆርጂያ ግዛት ከምትገኘው ደቡብ ምስራቅ ሳቫናህ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ