40 ሺህ ቬንዙዌላውያን ወደ ትሬኔዳድ እና ቶቤጎ ተሰደው አስቸጋሪ ህይወት እየመሩ ነው- ቢቢሲ

4 ሚሊየን ቬንዙዌላውያን ሀገሪቱ በገጠማት የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ሀገራቸውን ጥለው መሰዳዳቸው ተነገረ፡፡

40 ሺህ የሚሆኑት ትሬኔዳድ እና ቶቤጎ ወደተባሉት የካሪቢያን ደሴቶች ተሰደው አስቸጋሪ ህይወት እየመሩ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የአከባቢው ማህበረሰብ ተሳዶቹን በክፉ አይን ማየታቸው ሀገራቸውን ጥለው ለወጡት የቬንዙዌላ ዜጎች  አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቁ ማድረጉን በስፍራው ቅኝት ያደረገችው የቢቢሲ ዘጋቢ ተናግራለች፡፡

ከመከራ ወደ መከራ ነው የተሸጋገርነው የሚሉት ስደተኞቹ፤ ምግብ ለማብሰል አልጋቸውን እስከመማገድ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌሎቹም ወሳኝ የማህበራዊ ግልጋሎቶች በሚኖሩባቸው የካሪቢያን ደሴቶች እየተገለሉ መሆኑን ስደተኞቹ ገልፀዋል፡፡

ቬንዙዌላ ከአለም የመጀመሪያዋ ነዳጅ ላኪ ለመሆን ስታደርገው የነበረው ጥረት ከሀያ አመት ወዲህ በመንግስት አባክኝነት የተነሳ ወደ ኢኮኖሚው ቀውስ ገብታለች፡፡

ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የተንሰራፋው ከፍተኛ የሙስና ቅሌት አሁን ላይ 94 በመቶ የሀገሪቱን ህዝብ በድህነት እንዲኖር አስገድዷል፡፡