የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሀዋሳ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል አስመረቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ12 ሚሊየን ብር ያስገነባውን የሓዋሳ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል አስመረቀ።

የኢትዮጵያ የምርት ገበያ ለዋልታ በላከው  መግለጫ እንደገለጸው የሀዋሳ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕከል  ታህሳስ 6፣ 2011 ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ማዕከሉ ከመስከረም 21 ቀን 2011 ጀምሮ የሙከራ አገልግሎት የጀመረ ሲሆን፥  ከመስከርም ወር 21 እስከ ህዳር 21ቀን 2011 ዓ.ም  ባሉት ጊዚያት  22 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 315 ቶን  የቡና ምርትን  ማገበያያት  ችሏል ።

1 ሺህ 380 ካሬ ሜትር ላይ ግንባታው ያረፈው ማዕከሉ  12 ሚሊየን ያህል ብር ወጭ  የተደረገበት ሲሆን፥ 7 ነጥብ 76 ሚሊንዮን ብሩ በኢትዮጵያ  ምርት ገበያና  ቀሪው 4 ነጥብ 87 ሚሊየን ብር ከአውሮፓ ህብርት  መሸፈኑም ገልጿል።  

ማዕከሉ 90 ደንበኞችን በአንዴ ማስተናገድ የሚችል ሲሆን 40 የኤሌክትሮኒክስ ማገበያያ ኮምፒዩተሮች  ተገጥሞለቷል ።

የዘመናዊ የግብይት ሥርዓትን  ለማስፋፋት እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ኤሌክትሮኒክስ ግብይት ዘዴ  ከተሸጋገረ 3ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል።

የምርት ገበያው የግብይት ዘዴ  ታማአኒነት፣ ግልጽነትና ቅልጥፍናን ከመጨመሩ በላይ  የመረጃ አያያዙን ዘመናዊ  እንዲሆን ማድረጉን  ገልጿል ።