ከመሬት ጋር የምትመሳሰል ፕላኔት ማግኘታቸውን ሳይንቲስቶች ገለፁ

አዲሲቷ ፕላኔት ከምንኖርባት መሬት በአራት የብርሃን አመታት ርቀት ላይ የምትገኝ ነች፡፡ 
ፕሮክሲማ ቢ የመኖሪያ አካባቢ ልትሆን እንደምትችል በሳይንቲስቶቹ ተስፋ ተጥሎባታል፡፡

በብሪታንያ ተመራማሪዎች የሚመራው የአውሮፓ ሳይንቲስቶች ቡድን እንደሚለው በመጠን ከመሬት ጋር የምትመሳሰለው ፕሮሲማ ቢ ፕላኔት ለፀሀይ የምትቀርብና በኮከቦች ዙሪያ የምትሽከረከርናት፡፡

ተመራማሪዎች የፕላኔቷን መኖር ያረጋገጡት ለ16 አመታት በሰበሰቡት መረጃ እንዲሁም ቺሊ ላይ በገጠሙት ቴሌስኮፕ ከኮከቦች የሚወጣውን ብርሃን በመቆጣጠር ነው፡፡

ፕሮክሲማ ቢ ከመሬት 1.3 እጥፍ ትገዝፋለች፡፡ ኦርቢቶች በ11 ቀናት ልዩነት ይዞሯታል፡፡

ከመሬት ጋራ የሚያመሳስላት ብዙ ነገር ሊኖር ቢችልም በጣም ሞቃት ትሁን ቀዝቃዛማ  ብሎም ለህይወት አስፈላጊ የሆነው ውሃ በፕላኔቷ ስለመኖሩ እስካሁን የደረስንበት ነገር የለም ብለዋል፡፡  (ምንጭ : አልጃዚራ )