ፌስቡክ ከደንበኞቹ ክፍያን በቢትኮይን ሊቀበል መሆኑን አስታወቀ

ፌስቡክ በቢሊዮን ከሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ ደንበኞቹ የሚያገኘውን ክፍያ ከተለያዩ የክሪፕቶከረንሲዎች መካከል አንዱ በሆነው በቢትኮይን ለመቀበል እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ቢትኮይን እኤአ በ2009 በሳይንቲስቶች የተፈጠረና ዓለም አቀፍ የሆነ ዲጂታል የኢንተርኔት ገንዘብ ነው፡፡

ይሄውም ሰዎች በፈለጉት ጊዜ ከስልካቸው በመላላክ ሊገበያዩበት የሚያስችል ዓለማቀፍ የገንዘብ አይነት ነው፡፡

አንድ ቢትኮይን በዛሬ ገበያ 9 ሺህ 195.00 ምንዛሪው የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በኢትዮጵያ ብር 267 ሺህ 574.50 ነው፡፡

ፌስቡክ የክሪፕቶከረንሲ ዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለመተግበር የተነሳው ገንዘቡን በማይዋዥቅና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ እስካሁን እያገለገሉ ላሉት እንደማስተር ካርድ ያሉ “ክሬዲት ካርዶች” የሚፈፀመውን ክፍያ ተጨማሪ አማራጭ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

አዲሱ የክፍያ ስርአት ቀላል አማራጭ እንዲሆንም የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በካሊፎርኒያ በተደረገው የሶፍትዌር አበልፃጊዎች ኮንፈረንስ ላይ ጠቅሷል፡፡

በተለይም ፌስቡክ ቢትኮይንና ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግለውን ብሎክቼይን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጠንካራ ዳታ ሲስተም እንዲኖረው አቅዷል መረጃዉ የዴይሊሜይል ነዉ፡፡