“ካካሄድነው ጥናትና ምልከታ በመነሳት በመጪው ጊዜ የአለም የኢኮኖሚ እድገት በግለሰቦች የፈጠራ-ስራ መስፋፋትና የመማር ችሎታ ላይ የተመረኮዘ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ይህም የሚሆነው አዳዲስ ስራ-ፈጣሪወች በራስ መተማመናቸውን በማሳደግ ፣ ለሌሎች ስራ በመፍጠርና እንዲሁም ስራቸውንና ፈጠራቸውን አለም-አቀፍ በማድረግ ነው” ሲሉ የቢ20 የስራ-እድል ቡድን ዋና-ጸሀፊ (B20’s Employment Taskforce) የሆኑት በኮርን ፌሪ (Korn Ferry)ጋሪ ዲ ቡርኒሰን በ አመታዊው የስራ-እድል ቡድኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው የቢዝነስ 20 (ቢ20) ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡
የስራ-እድል ቡድኑ ባወጣቸው ዋና-ዋና የሆኑ 4 ነጥቦች (ምክሮች) ላይ በአጽንኦት የተናገሩት ቡርኒሰን “የስራ-ፈጠራን መርሆወችና መተግበር አዋጭ በሆነ መልኩ መተግበር ፣ በሀብታምና ድሀ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ፣ እንዲሁም በሁለቱ ጾታወች መካከል ያለውን የስራ-እድል ልዩነትና የገበያና የሰራጠኛ አለመጣጣምን” አስመልክተው ተናግረዋል፡፡
“አሁን ልናደርገው የሚገባን ተግባር እነዚህን ምክሮች ብልህ በሆነ መልኩ መተግበር እንዲሁም ለአዳዲስ የስራ-ፈጣሪወች እንዲሁም ለመጭው ጊዜ ቀጣሪወችና ተቀጣሪወች ማስተማር ነው” ብለዋል፡፡
እንደ ቡረኒሰን ገለጻ በሁሉም የአለማችን ክፍል ከና ያልተነካ የስራ-ፈጠራ እምቅ-ሀብት አለ፡፡ አስፈላጊውን አቅርቦት ብናሟላላቸው ብዙወቹ ይማራሉ፡፡ “ዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት ወጣቱን ወደ ስራ-ፈጣሪነት መስክ ለማስገባት አበይትና ሁነኛ መንገድ ነው” ብለዋል፡፡ ወደዲጂታሉ አለም መግባትም እንዲሁ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የአለም-ክፍሎች ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ይህም አቅም ያላቸው ስራ-ፈጣሪወች ቤታቸው ቁጭ ብለው ጥሩ የሚባል የእውቀት ሽግግር ያካሂዳሉ፡፡ በኢንተርኔት የቀጥታ ስርጭት (ኦንላይን) የሚተገበሩ የ እድገት እቅዶች በሀብታምና ድሀ እንዱሁም ሴትና ወንድ መካከል ለሚታየው ክፍትት መልስ ሊሆን ይችላል፡፡
እንደ ቡረኒሰን ገለጻ ብልህ የሚባሉ የእድገት እቅዶች በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው፡፡ “ቡድኑ በሀገራ በኩል የሚጣዩ አላስፈላጊ የቢሮክራሲ መንዛዛቶችን ለማስቀረት የስራ-ሂደት ማሻሻያወችን እንደ መፍትሄ አቅርቧል፡፡ በአለም-አቀፍ ደረጃ ከ3.2 ቢሊዮን የሚልቁ ሰወች በአሁኑ ጊዜ በኢንተርኔት የመረጃ-መረብ ተገናኝተዋል፡፡ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ከገበያው ጋር የሚጣጣሙ የስራ-ዘርፎችንና ሰራተኞችን ማግኘት ይቻላል” በማለት ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠልም ቡርኒሰን በመማርና በእውቀት እድገት ላይ መስራትን እንደ አንድ ውጤታማ መንገድ አስቀምጧል፡፡ “ጥሩ የሚባል የመማር አቅም ከልምዶች በቀላሉ መማርንና የተማሩትንና እንዲሁም የተገነዘቡትን ነገር በአጥጋቢ ሁኔታ ወደተግባር መቀየር ነው” በማለት ያብራራል፡፡
ኮርን ፌሪ ለበርካታ አስርተ አመታት ሰራተኞችን በማብቃትና ችሎታቸውን በማሳደግ በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ይሄን ተግባር ቡረኒሰን ሲያብራራ “በቅርብ ጊዜ ያወጣነው በኢስያ-ፓስፊክ ላይ ያጠነጠነው ስኛታችን እንደሚያሳየው ከሆነ የጾታ ስብጥራቸው ከፍተኛ የሆኑት ድርጅቶች ከፍተኛ የስራ ሁጤት አሳይተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡ እ.ኤ.አ 2014 ቢያንስ 10 ፐርሰንት ያህል ሴት ሰራተኛ ያላቸው ተቋማት 14.9 ፐርሰንት እድገት ሲያስመዘግቡ ከዚያ ያነሰ የሤትሰራተኛ ቁጥር ያላቸው ግን 12.6 ፐርሰንት ገረማ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ቡሪሰን አክለውም ቻይናውያን ድርጅቶች ቡድኑ ለሚያዘጋጀው የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲሁም የድጋፍ ሰነዶች ዝግጅትን በተመለከተ አበይት የሚባል ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡ እንዲሁም ጥቂት የማይባል መረጃ ከቻይናውያን ድርጅቶች እና የዘርፉ ማህበራት በቅርብ አመታት ሊተገበር ይችላል ብለዋል፡፡ አንዱና ወሳኙ ነገር ያላሳለሱ አበረታች ጥረቶች የተካሄዱ ሲሆን ችግሮችንም በመፍታ በኩል እንዲሁ ያላሳለሰ ስራ ተሰርቷል፡፡ “ቻይናም እንዲሁ ምንም እንኳን ሰፊና በአይነትም የበዛ የመልክአ-ምደራዊ አቀማመጥ ቢኖራትም መሰል ውጤት አስመዝግባለች ይሄም ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሳሰረና የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የውሳኔ ሰጭነት ተግባር ለኢኮኖሚዊ የሚኖረውን ሚና በትልቁ ያሳያል” ብለዋል፡፡
“የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ቻይናውያን የግሉ ሴክተር ባለሀብቶች በአለም-አቀፉ መድረክ ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡ ሁዋዌ ፣ ዥያወሚ ፣ አሊባባ እንዲሁም ባይዱ በአኑ ጊዜ በአለም-አቀፍ ደረጃ የታወቁ ታላላቅ የምርት መለያወች ዎነዋል እንዲሁም አሊፔይን የመሳሰሉት አዳዲስ መስኮችን በተመለከተ እንደ-ጥናታ መስጫነት ያገለግላሉ፡፡ እንደኔ አስተሳሰብ ይሄን መሰል ተግባሮች በርቱ መባል ያለባቸው ሲሆን ለቻይናውያን ድርጅቶችም እንዲሁ በተለያዩ ዘርፎች ላይ እንደ ምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ እንዲሁም አለምን በመገንባት በኩል ውጤታማና አዋጪ ተቋማት ናቸው” በማለት ተናግረዋል፡፡ (ፒፕልስ ዴይሊ)