አርጀንቲና እና ቻይና   አራት መስኮች ላይ ለመተባበር ተስማሙ 

ቻይና እና አርጀንቲና ወደ እድገት በሚያደርጉት ጉዞ በትብበር መስራ አለባቸው ሲሉ የአርጀንቲናው ፕሬዝዳነት ማውሪሲወ ማክሪ ለፒፕልስ ዴይሊ ረቡ ዕለት ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀገሪቱ ከቻይና ጋር ያላትን ትብብር ማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳነት ማውሪሲወ ማክሪ ይህን የተናገሩት በመስከረም ወር መጀመሪያ በምስራቃዊ ቻይና በዝጂንግ ግዛት ለሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ (G20 Summit) ከመሳተፋቸው በፊት ነው፡፡

ፕሬዝዳነቱ በተጨማሪም በመስከረም ወር መጀመሪያ በቻይና የሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ እንደዋነኛ የአለም-አቀፍ መሪወች መሰብሰቢያ መድረክ ዘላቂናት ያለው እንዲሁም ሁሉን-አቀፍ እድገትን ለማጠናከር አበየት ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ 

“የቡድን 20 ስብሰባ የዘመናዊው አለም እየተፈተነባቸው ያሉትን ችግሮች ለማቅረፍ ትልቅ ሚና ኖረዋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል፡፡ 

ከቻይናው ፕሬዚዳን ዢ ጅንፒንግ ጋር በዋሽንግተን በተካሄደው የኒውክለር ደህንነት ስብሰባ (Nuclear Security Summit) ላይ መገናኘታቸውን ያወሱት ፕሬዝዳንቱ ከቀናት በኋላ በሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ከፕሬዚዳን ዢ ጋር በመገናኘት የሁለቱን ሀገራት ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት እንዲሁ አሳውቀዋል፡፡ አክለውም “ከቻይና ጋር ያለንን ወዳጅነት ማጠናከር በተለይ በጣም ጠቃሚ ነው” ብለዋል፡፡ 

ቻይና እና አርጀንቲና በእድገት ጎዳና ተመጋጋቢ የሚባል ጠቀሜታ ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም አርጀንቲና ቻይና በምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ዙሪያ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ትልቅ ጠቀሜታ ይራታል፡፡ የቻይና የመሰረተ-ልማት እድገትና ማስፋፋት እንዲሁም ሀገሪቱ በመሰረተ-ልማት ግንባታ በኩል የሳየችው እንቅስቃሴ እንዲሁ ለአርጀንቲና ትልቅ ትምህርት ይሆናል ብለዋ፡፡ 

ፕሬዝዳንቱ እንዲሁ በቱሪዝምና ስፖርታዊ መስኮች ዙሪያ ሀገራቸው ከቻይና ጋር መስራ እንደምትፈልግ አስታውቀዋል፡፡ "በመጭወቹ ጊዜያት አያሌ የሚባል ቻይናውያን ጎብኝወችን (ቱሪስቶችን) ወደ ሀገራችን እንደምንስብ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል፡፡ መረጃን በማስደገፍ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ከ100 ሚሊዮን የሚልቁ ቻይናውያን በየአመቱ ከሀገራቸው ውጭ ለጉብኝት የሚሔዱ ሲሆን ከዚህ አሀዝ ውስጥ 30,000 ያህሉ ብቻ አርጀንቲናን በአመታሁ ሁናቴ ይጎበኛሉ ብለዋል፡፡

የስፖርቱን ዘርፍ በተመለከተም እንዲሁ የትብብር ልውውጦች ተቀሜታ እንዳላቸው አውስተዋል፡፡ እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ አርጀንቲና የተሻለ የሚባል ደረጃ ላይ ለች ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቻይና ውስጥ እያደገ የመጣው አፍቅሮተ – እግር ኳስ እንዲሁ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳነት ማክሪ በተጨማሪም የቻይና-ላቲን አሜሪካ የትብብር ፈንድን ያደነቁ ሲሆን አርጀንቲና ከቻይና ጋር የሚደረጉ ማናቸውንም ስትራቴጅካዊ የትብብር መድረኮችን እንደምትደግፍ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም መሰል ትብብሮች ስራ-ፈጠራን የሚበረታቱ ሲሆን በሁለቱም ሀገሮች የስራ እድሎችን ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡
አርጀንቲና ቀጣዩንና በ2018 የሚካሄደውን የቡድን 20 ስብሰባ ታዘጋጃለች፡፡ ስብሰባውን ማዘጋጀት ለሀገሪቱ ፈተና ሊንሆ እንደሚችል የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው ከቻይና ጋር ድህነትን በማጥፋት ፣ የትምህርት አቅርቦትን በማሳደግ ፣ እንዲሁም የአለም አቀፍ መተባበርን በማስፋፋት ዘርፎች እነደምትሰራ ተናግረዋል፡፡ (ፒፕልስ ዴይሊ)