በግማሽ አመት የኦንላይን ግብይት የቻይና ኢኮኖሚ እምርታ ማሳየቱ ተገለጸ

OSAKA, June 29, 2019 (Xinhua) — Chinese President Xi Jinping meets with U.S. President Donald Trump in Osaka, Japan, June 29, 2019. (Xinhua/IANS)

በግማሽ አመት የኦንላይን ግብይት የቻይና ኢኮኖሚ እምርታ ማሳየቱ  ተገለጸ፡፡

የኦንላይን ግብይት ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ እየተጫወተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ባለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት የኦንላይን ግብይት የግማሽ አመት የቻይና ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ እንደነበር የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል፡፡

የአለም ሁለተኛዋ ባለ ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ባለቤት ቻይና ለኢኮኖሚዋ እድገት የሃገሪቱ ግዙፍ የማኑፋክቸሪንግ አምራች ሴክተሮች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ አሁን ደግሞ በሃሪቱ ያሉት የኦላንይን የኢ-ኮሜርስ ኩባንያዎች ለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከቱ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡

ከእነዚህ የኢ-ኮሜርስ ወይም የድረገፅ መገበያያ ተቋማት ዉስጥ ግዙፉ የአሊባባ ኩባንያ ተጠቃሽ ነዉ፡፡ የአሊባባ ኦንላይን ግብይት ቸርቻሪ የሆነዉ ቲ ሞል የ150 ሚሊዮን ሸማቾች ትእዛዝ ተቀብሏል፡፡

የስታስቲክስ መረጃ እንደሚያመላክተዉ ከ8 ኦንላይን የግብይት ጥያቄዎች አንዱ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሲሆን ሽያጩም ከ40 የተለያዩ መለያ ያላቸዉ ምርቶች ከ100 ሚሊየን በላይ የቻይና ዩአን ገቢ አስገኝተዋል፡፡

በባለፉት ዓመታት በፍጥነት በማደግ ላይ የነበረው የቻይና ኢኮኖሚ በዚህ በኢንተርኔት ኦንላይን መገበያያ ተመራጭ የግብይት ዘዴ መደገፉም ይነገራል፡፡

እንደ አፕል ያሉ ታዋቂ መለያ ያላቸዉ ምርቶች 170 በመቶ ዓመታዊ እድገት እያሳዩ መምጣታቸዉ ለሃገሪቱ ምጣኔ ሀብት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ የሃገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር ባወጣዉ የግማሽ አመት ኢ ኮሜርስ መረጃ ገጠራማ የቻይና አካባቢዎች የታየዉ የንግድ እንቅስቃሴ 1.3 ትሪሊዮን ዩአን የደረሰ ሲሆን በየአመቱ የ30.4 በመቶ እድገት እያስመዘገበ መጥቷልም፡፡

በቻይና ያሉ የኢ ኮሜርስ ኩባንያዎች በአጠቃላይ ባሳለፍነዉ ግማሽ አመት 31.36 ትሪሊዮን ዩአን ገቢ አስገኝተው፤ 8.5 በመቶ የእድገት መጠንም አሳይተዋል፡፡

በ2019 መጨረሻ በተያዘዉ ግብ ቢያንስ 10 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት ለማላቀቅ ሃገሪቱ አቅዳ እየሰራች እንደሆነም የ ሲ ጂቲኤን ዘገባ ያሳያል፡፡