የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራርና አባላት የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄዱ

ከ600 በላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል፣ ጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራሮችና አባላት ለሀገር ህልውና ሲሉ መስዋትነት ለከፈሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር በመግለጽ የደም ልገሳ መርኃግብር አካሄዱ፡፡

የጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬቱ የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ በሚደረገው ጥረት የፖሊሳዊ ግዴታቸውን ከመወጣት ጎን ለጎን ደም ከመለገስ ጀምሮ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።