ፕሬዳዝንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብንት አቢጃን ገቡ

የኢፌዴሪ ፕሬዳዝንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብንት ኮቲዲቯር አቢጃን ገብተዋል፡፡

ለፕሬዝዳንቷ በአቢጃን ከተማ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ በኮትዲቯሩ ፕሬዝዳንት አላሳኔ ኦታራ በአለ ሲመት ላይ ለመገኘት ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በኮትዲቯር ቆይታቸው ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በምዕራብ አፍሪካ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት እንደሚያርጉ ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::