ኬንያ 24 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ለመግዛት አዘዘች

ኬንያ 24 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ለመግዛት ማዘዟን ስታር ጋዜጣን ጠቅሶ ቢቢሲ በዘገባው አመለከተ።

የኬንያ መንግስት ለክትባቱ 10 ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ (89 ሚሊየን ዶላር) ለክትባቱ መመደቡን የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር የስራ ሃላፊዎች ለጋዜጣው ገልጸዋል።

ለግሎባል የክትባት ህብረት ኢኒሽዬቲቭ (ጋቪ)ሚኒስቴሩ ጥያቄውን ባለፈው ሳምንት ማቅረቡም ተገልጿል።

የታዘዘው የክትባት መጠን የአገሪቱን ህዝብ 20 በመቶ ያህል መሸፈን የሚችል መሆኑ የተነገረ ሲሆን አረጋውያንን ጨምሮ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቅድሚያ በመስጠት ክትባቱን ያገኛሉ።

ጋቪ ከዚህ ቀደም በገለጸው መሰረት አንድ የኮቪድ-19 ክትባት ወጪ እስከ ሶስት ዶላር ድረስ ይሆናል።