ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ዴኒያ ጋይሌ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ መንግስት በትግራይ ክልል ስለወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ ንጹሃንን በጠበቀ መልኩ ዘመቻው መከናወኑንም አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም የስነ ህዝብ ፈንዱ በሱዳን ላሉት ሴት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ድጋፍ በማድረጉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
መንግስት ህግ የማስከበር ስራውን በፍጥነት አጠናቆ አሁን ላይ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እየሰራ መሆኑንም አውስተዋል፡፡
እንዲሁም መንግስት አሁን ላይ በትግራይ ክልል እያደረገ ስላለው ሁሉን አቀፍ ሰብአዊ እርዳታ በተመለከተም ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ዴኒያ ጋይሌ በበኩላቸው፥ ፈንዱ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ሴቶችና ሕፃናት የተጠናከረ ድጋፍ ለመስጠት እንዳቀደ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡