መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከአካባቢ ሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለው ነው – ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ

መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከአካባቢ ሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

“ሁለቱ ሀገራት እንዲህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁሌም የውይይትን አማራጭ የሚከተሉ በመሆናቸው ክስተቱ የሁለቱን ሀገራት ጥብቅ ትስስር አያላላውም” ብለዋል ጠቅላይ ሚስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፡፡

“ክስተቱን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደው በማራገብ ልዩነትን ለማስፋት የሚጥሩ አካላት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡