አልሸባብ የኬኒያ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ማውደሙ ተገለጸ

በምስራቅ ኬንያ ጋሪሳ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት መግቢያ

የአልሸባብ ወታደሮች በሶማሊያና በኬኒያ ድንበር በምትገኘው ኢሌሌ ማንዳራ አካባቢ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ላይ ጥቃት ማድረሱን የኬኒያ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ጥቃቱ የደረሰው በኬኒያ የቴሌ ኮሚኒኬሽ አገልግሎት በሚሰጠው ሳፋሪ ኮም በተባለው የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት ላይ እንደሆነ ነው የተነገረው ፡፡

ሶማሊያንና ኬኒያን በሚያዋስነው ማንደራ በሚባለው አካባቢ የቴልኮም መሰረተ ልማት በቦንብ ማውደሙን የሰሜን ምስራቅ ኬኒያ ክልላዊ የፖሊስ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ሮኖ ቡኔ ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው የቴሌኮም ግንኙነት በአሸባሪው ምክንያት መቋረጡንና ፖሊስ ክትትል እያደረገ አንደሆነ ነው ኮማንደሩ የገለፁት፡፡

የአልሸባብ ቡድን የጥቃት ኢላማ የሚያደርገው በኬኒያ በሰሜን ምሰራቃዊ ክፍል በሚገኙ ጋሪሳ፤ ማንደራ፣ ዋጂር በሚባሉ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በአካባቢው በሚኖሩ ሰዎች የጥቃት ኢላማ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

የሽብር ቡድኑ ጥቃቱን የፈፀመው በማንዱራ ከአራት ቀን በፊት አዲስ የፖሊስ ቢሮና ቤቶች ከተገነቡ በኃላ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ኬኒያ ከሱማሌ ላንድ ጋር ባደረገችው ጥብቅ ግንኙነት መቋደሾ ከናይሮቢ ጋር ያለትን   የዲፕሎማሲ ግንኙነት ካቋረጠች በኃላ የደረሰ ጥቃት እነደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካ አስነብቧል፡፡

አልሸባብ እ.ኤ.አ በ2006 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆነ ኬኒያ ላይ በተደጋገሚ ጥቃት አድርሷል፤የሽብር ቡድኑ የመገናኛ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በማድረሱ ይታወቃል ፡፡

(በምንይሉ ደስይበለው)