ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ ፡፡

ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

ስድስት ኪሎ አካባቢ ለሚገነባው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ተካሄደ።

በዚህ የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ፕሮግራም ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ጌዛሊ አባሲማል እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

አዲስ የሚገነባው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ 13 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን ለግንባታው 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተመድቧል። (በሳራ ስዩም)