በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታኅሣሥ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ክልል አቀፍ ፈተናው በ5 ሺህ 162 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ከትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ጠቅሷል፡፡

የፈተና ቁሳቁስ ተሟልተው ክልል አቀፍ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ገልፀዋል፡፡

ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱንም ተናግረዋል፡፡

በመደበኛ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ415 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አብመድ ዘግቧል፡፡