በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ባደረሱ 42 ፀረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ ተደምስሰዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃም ጸረ-ሠላም ኃይሎች ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና እና ቀስቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።