አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተመድ በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ህጻናት ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተመድ በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ህጻናት ልዩ ተወካይ ቨርጂኒያ ጋምባ ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ታዬ በውይይታቸው በትግራይ ክልል ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ ለልዩ ተወካይዋ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በህወሓት በኩል ህጻናትን ለጦር የመመልመልና ህጻናት ወታደሮችን የመጠቀም ጉዳይን በተመለከተ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡