የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በባህር ዳር በሚገኘው ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆስፒታል የማድረግ እንቅስቃሴን ጎበኙ፡፡
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ገፃቸዉ እንደገለፁት በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ የጤና መዛግብት አፈፃፀም እና የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ህሙማንን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሰራውን ስራም ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅትም በቁርጠኝነት የሚሰሩ የሆስፒታሉንና የክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮችንና ሰራተኞችን አመስግነዋል፡፡