በአሚሶም ሴክተር ሶስት ሰላም ማስከበር ተልኮ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ስድስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ዘማቾች ሜዳይ ተሸለሙ፡፡
የሜዳልያውን የሴክተር ሶስት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አለሙ አየነ እና የ7ኛው ዙር ሰላም አስከባሪ አዛዥ ብ/ጄ ዘውዱ ሰጥአርጌ አልብሰዋል።
ብ/ጄ አለሙ አየነ በስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ፣ መንግስትና ህዝባችን በከሃዲው ጁንታው እና በሌሎች ግብሮአበሮች ላይ በአጭር ግዜ ህግን በማስከበር ውጤታማ ኦፕሬሽን ተካሄዷል፤ ህገ መንግስቱም ተከብሯል፡፡
መንግስትና ህዝባችን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያስመሰከሩበት፣ በታሪክ ታላቅ ገድል የተፈፀመበት ነው ብለዋል፡፡
ብ/ጄ አለሙ አባላቱ ፣ ተልዕኳቸውን ሃላፊነት በተሞላው መንፈስ የአፍሪካንና የአገራቸውን ክብር በማስጠበቅ በድል እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡