በመቐለ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ

 

በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት በመቐለ ከተማ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሀይለስላሴ አስታወቁ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ከዛሬ ከሰአት በሁዋላ ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከንቲባው ገልፀዋል።

የከተማዋ ነዋሪና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረትም የባንክ አገልግሎቱ ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸው  ነው የተገለፀው።

የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል። (ምንጭ ፡- ኢፕድ)