በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሊተዋወቁ እንደሚገባ ተገለጸ

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር በዘርፉ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማሳወቅ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በቀጣይ 10 ዓመታት በዘርፉ ያሉ ዕድሎችን ለመጠቀም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በጥናት የተለዩ አካባቢዎችን ማስተዋወቅ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ በማዕድን ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ አቅምና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰብ እና ተቋማት መሠማራት እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ቤተ ሙከራ፣ ጉድጓድ ቁፋሮ እንዲሁም ወርቅ ማጣሪያ ለማቋቋም በጋራ መሥራት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

በኢትዮጵያ በነዳጅና ጋዝ ፍለጋ ዘርፍ የተሠማሩ 3 ኩባንያዎች እንዳሉም ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ 63 የሚደርሱ በማዕድን ዘርፍ የተሠማሩ ድርጅቶች ፈቃድ ማቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡
(በሰሎሞን በየነ)