በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ በክልሉ የተደረገውን የህግ ማስከበር ተከትሎ መቀሌና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ያስመረቁ መሆኑን ገልጸው የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 07/2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ መደረጉን ተናግረዋል።
በቀጣይም የመቀሌና አዲግራት ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በሚቻልበት ሁኔታና ለተቋማቱ መደረግ ባለባቸው ድጋፎች ላይ ውይይትና የስራ ክፍፍል ተደርጓል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በህግ ማስከበር ወቅት የደረሰውን ጉዳት ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ ከተማሪዎችና የዩኒቨርሰቲዉ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡