አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና አምስት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በተጨማሪ በዞኑ ጃል ያዴሳ ለተባለ የኦነግ ሸኔ አባል በባንክ በኩል ሊላክ የነበረ 122 ሺህ 950 ብር ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቄለም ወለጋ ዞን እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመግታት የኅብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ የኦሮሚያ ፖሊስ በትጋት እየሠራ እንደሆነ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡