አንጋፋው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ሕይወቱ አለፈ

አንጋፋው የአሜሪካ የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በ87 ዓመቱ በኮቪድ-19 ሕይወቱ ማለፉ ተገለጸ።

ከ60 ዓመታት በላይ በሚዲያው ላይ የቆየው ላሪ ኪንግ በተለይ ለ25 ዓመታት በሲኤንኤን ቴሌቪዥን ሲያዘጋጅ በቆየው የራሱ ፕሮግራም ይታወቅ ነበር።

በዚህ ፕሮግራሙ ለበርካታ ትላልቅ መሪዎች፣ ዝነኛ ሰዎች እና ታዋቂ አትሌቶችን ቃለ-መጠይቅ አድርጓል።

ለረጅም ዓመታት በቆየበት ሙያው በርካታ ሽልማቶች እና እውቅናዎችን ያገኘው ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል የገባው ባለፈው ወር እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።