የኮቪድ-19 ክትባት የቫይረሱን ስርጭት እንደሚቆጣጠር ማረጋገጫ ለእንዳልተገኘ ተገለፀ

የኮቪድ-19 ክትባት የቫይረሱን ስርጭት ይቆጣጠራል የሚል ማረጋገጫ እንዳልተገኘለት ተገለፀ፡፡

በመሆኑም ክትባቱን በመተማመን ከዚህ በፊት ሲደረጉ የነበሩ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊቆሙ አይገባምም ተብሏል፡፡

የኮቪድ ክትባትን የሚወስዱ ሰዎች የቫይረሱን ስርጭት ከማስቆም ይልቅ የስርጭቱን መጠን ሊጨምሩት ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

ሰዎች የኮቪድ ክትባትን ቢወስዱም ቫይረሱን ለሌሎች ሊያሰራጩ ይችላሉና ቫይረሱን ለመከላከል የሚወሰዱ ጥንቃቄዎች ሊቋረጡ አይገባም ሲሉ አንድ የእንግሊዝ የህክምና መኮንን አስጠንቅቀዋል፡፡

ባለሙያው ተመራማሪዎች አሁንም የተመረቱት ክትባቶች የቫይረሱን ስርጭት ከማስቆም አንፃር ያላቸውን ሚና አጥንተው አልደረሱበትም! ቫይረሱን መቶ በመቶ ይከላከላል የሚል ማረጋገጫ የተሰጠው አንድም ክትባት የለምም ብለዋል፡፡

በመሆኑም ክትባቱን በመተማመን ከዚህ በፊት ሲደረጉ የነበሩ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊቆሙ አይገባም፡፡ የእንቅስቃሴ ገደቦቹም ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይ የመጀመሪያው ዙር ክትባት በተወሰደበት የመጀመሪያዎቹ አንድና ሁለት ሳምንታት ውጤቱን ማወቅ ከባድ በመሆኑ ቢያንስ ሶስት ሳምንታትን መጠበቅ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

አንድ ሰው ሁለቱንም ዙር ክትባት ቢያገኝም እንኳን ቫይረሱን ለሌሎች የማስተላለፍ እድል ሊኖረው እንደሚችልም ነው የህክምና ባለሙያው የተናገሩት፡፡

ክትባቱን ወስጃለሁ በሚል ለቫይረሱ የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን የሚያቋርጡ ሰዎች ለራሳቸው እንዲሁም ለሌሎችም ስጋት መሆናቸው አይቀሬ ነው ሲሉም ያስጠነቅቃሉ፡፡

በእግሊዝ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ለመውሰድ ሶስት ሳምንታት ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ወደ 12 ሳምንታት ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ለሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ለማዳረስ ነው፡፡

በእንግሊዝ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከሶስት ሚሊየን አልፏል፡፡

97ሺ 329 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡