ሰላም ለአንድ ሀገርና ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋና መሰረት ነው – አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

 

\

ሰላም ለአንድ ሀገርና ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋና መሰረት በመሆኑ የእነዚህን ችግሮች ምንጭና ምንነት ከስሩ ማየትና መፈተሽ ያስፈልጋል ሲለ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።

“እርቀ ሰላምና መረጋጋት ለፍትሐዊና ዲምክራሲ ስርአት ግንባታ የድህረ ለውጥ ተግዳሮቶችና ስኬቶች” በሚል ርዕስ የሰላም ወግ የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ተካሂዷል።

የሰላም ሚኒስቴር ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ÷ ሰላም ለአንድ ሀገርና ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋና መሰረት በመሆኑ የእነዚህን ችግሮች ምንጭና ምንነት ከስሩ ማየትና መፈተሽ ያስፈልጋል ብለዋል ።

የጅንጅጋ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ በበኩላቸው÷ ከለውጡ በፊትም ሆነ ከድህረ ለውጡ ወዲህም እንደ ሀገር በርካታ የሚባሉ የሰላም እጦቶችና የግጭት ታሪኮቻችን በዘመናዊ መንገድ በዕርቀ ሰላም መቋጫ ሊያገኙ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

በመድረኩ ዘላቂ ሰላም እና ሀገራዊ መግባባትን ለማምጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

ከዚህ የሰላም ወግ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ የተለያዩ ሀሳቦች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።