6ኛ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ዙሪያ ከሲቪል ማህበራት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ የህግ አስፈፃሚ አካላት በምን መልኩ መደራጀት እና መስራት እንዳለባቸው ረቂቅ መመሪያው ማካተቱን ተናግረዋል፡፡
በምርጫ ወቅት የኮቪድ 19 ስርጭትን በመከላከል እንዲሁም የምርጫ ሂደቶች ፍፁም ሰላማዊ በማድረግ መራጩ ማህበረሰብ ነፃነት በሰፈነበት መልኩ እንዲመርጥ የፀጥታ ሁኔታው የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡
ጠቅላላ ምርጫው ነፃ፣ ገለልተኛ እና ፍትሀዊ እንዲሆን የሲቪል ማህበራት ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑም ተጠቁሟል::
(በሄብሮን ዋልታው)