በቄለም ወለጋ ዞን 8 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የኦሮሚያ ፖሊስ በቄለም ወለጋ ዞን በወሰደው የሕግ የበላይነት ማስከበርና ሰላምን የማረጋገጥ ስራ 8 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡

በዞኑ አንፍሎ ወረዳ፣ ዬቲ በሚባል ቀበሌ 2 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይም እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል፡፡

በጅማ ዞን ሊሙ ሰቃ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይት ተመተው ከቆሰሉ በኋላ ለማምለጥ ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ወንዝ ውስጥ ገብተው የ6 ታጣቂዎች አስከሬን ከወንዝ ውስጥ መገኘቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡