5ኛ ዙር ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን መሪነትና አዘጋጅነት በአራዳ ቴዎድሮስ አደባባይ በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በርካታ ነዋሪዎች ፣ የፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረጋላቸው እንግዶች ታድመዋል ።
´´ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ ፤ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ!“ በሚል መሪ ሀሳብ በከፍተኛ ንቅናቄ የተጀመረው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እንደቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል።
ቀጣዩ የስደተኛውን የማህበረሰብ ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማስተናገድ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ችቦውን ከአራዳ ክፍለ ከተማ ተረክቧል፡፡