የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ ነው

የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ በመስክ ጉብኝት ተገመገመ፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በስፍራው በመገኘት ገመገሙ፡፡

በግምገማቸውም መሰረት የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝ ተመልክተዋል፡፡

ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራተሮች፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።