በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጽ/ቤት የተገነባው የባንቆ ዳዳቱ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመረቀ

የካቲት 09፣ 2013 (ዋልታ) – በደቡብ ክልል ጌድኦ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት የተገነባው የባንቆ ዳዳቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በሁሉም ክልሎች በመጀመሪያው ዙር  ካስገነባቸው 20 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 3ቱ በደቡብ ክልል የሚገኙ ሲሆን 30 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው የባንቆ ዳዳቱ መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች፣ የቤተ ሙከራ እና ቤተ መጸሐፍትን ያካተተ ነው፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በደቡብ ክልል በሸካ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ያስገነባቸውን ቀሪ ሁለት ትምህርት ቤቶች በቅርቡ ያስመርቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

(በስመኝ ፈለቀ)