ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከኔዘርላንድስ ጠ/ሚ ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የካቲት 10/ 2013 (ዋልታ) – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ማርክ ሩት በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ነው የተወያዩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በውይይቱ ወቅት በቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ መምክራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኔዘርላንድስ ጋር በዲፕሎማሲ፣ በንግድ እና በኢንቨስትመንት በኩል ያላት የቆየ ግንኙነት ለቀጣይ ግንኙነት መሰረት ነው ብለዋል፡፡