ጠ/ሚ ዐቢይ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት አደረጉ

                     ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር  ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በትግራይ ክልል ስላለው ሰብአዊ ሁኔታ፣ የጸጥታ ጉዳዮች፣ መሰረተ ልማት፣ የህብረተሰብ አገልግሎት ጉዳዮችና ሌሎች ተግዳሮቶችን ገምግመዋል።

በትግራይ መፍትሔ የሚፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮች ተለይተው እርምጃ የሚወሰድበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡