ምርጫ ቦርድ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ምክክር አካሄደ

የካቲት 13/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት የእውቅና ሰርተፍኬት ከተሰጣቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ለመራጮች ትምህርት ለመስጠት እውቅና የተሰጣቸው 65 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት አባላት እና አመራሮች እየተሳተፉ ነው ተብሏል።