የሚኒስቴሮች የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

 

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ

የካቲት 15/2013 (ዋልታ) – የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በየስድስት ወሩ የምናካሂደውን እያንዳንዱን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሥራ ክንውን ግምገማ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር በመሆን ጀምረናል” ብለዋል።

በጸደቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቀጣይነት ያለውን ምዘና መከወናችን፣ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት እና አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ለዜጎች ተገቢው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል።