የካቲት 18/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የትምህር ውይይት ላይ ተሳትፋለች።
በመድረኩ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት የመማር ማስተማር ስራውን በቴክኖሎጂ በመደግፍ ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶች ዳግም ሲከፈቱም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች የሚተገበር የኮቪድ መከላከል ፕሮቶኮል በማዘጋጀት፣ ማህበረሰቡን ያሳተፈ “ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” ንቅናቄን በማድረግ መማር ማስተማር ስራውን ማስቀጠሏን አብራርተዋል።
የተለያዩ ሀገራትም ዳግም ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት ሲገደዱ ኢትዮጵያ ማህበረሰብን ባሳተፈ ስራዋ ውጤታማ ስራ መስራቷ በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡
በውይይቱ የትምህርት ዘርፍ የሰው ሃይል ልማት፣ ዝቅተና ገቢ ላላቸው ሰዎች፣ ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ትምህርትን በፍትሃዊነት ማዳረስ ላይም መምከራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡